ስሎቫኪያ በሃገሪቱ ውስጥ ተጠልለው ለሚገኙ የዩኩሬን ስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀንስ አስጠንቅቃለች ።
ማስጠንቀቂያው የተናገሩት የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ ናቸው።
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ራሺያ በዩኩሬን አድርጋ ወደ አውሮፖ ግዛት የሚሸጋገረውን የአምስት አመት ውል አይቀጥልም ማለቷን ተከትሎ ነው።
በዚህም የስሎቫኪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ፤በስሎቫክ ግዛት ለሚገኙ የዩክሬን ስደተኞች የሚሰጠውን እርዳታ እንደሚቀንስ አስፈራርተዋል።
የዩክሬን የመጓጓዣ ቱቦው ከሞልዶቫ, ሮማኒያ, ፖላንድ, ሃንጋሪ እና ስሎቫኪያ የቧንቧ መስመር ስርዓቶች ጋር እና ከዚያም ወደ ኦስትሪያ እና ጣሊያን ከሚሄደው ጋር የተቆራኘ ነው።
ስሎቫኪያ በጋዝ ፍሰቱ መቋረጡ ምክንያቱም 60 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ፍላጎት ለመሸፈን ትገለገል የነበረ ቢሆንም አሁን በመቋረጡ ቁጥር አንድ ተጎጂ እሷ በመሆኗነው ተብሏል።
ልኡል ወልዴ
ታኀሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
