በካሊፎርኒያ ፉለርተን ከተማ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
አደጋውን ተከትሎ የፉለርተን ከተማ ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ከሞቱት በተጨማሪ በ19 ሰዎች ተጎድተዋል፡፡
ተጎጂዎቹ በመኖሪያ መንደር ዉስጥ ያሉ ሳይሆኑ እንዳልቀረ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
አደጋዉ የደረሰዉ አዉሮፕላኑ በረራ ከጀመረ ከ ሁለት ደቂቃ በኋላ ነዉ ተብሏል፡፡
አባቱ መረቀ
ታኀሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
