የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የእርድ አገልግሎትና ስጋ ስርጭት የስራ ሂደት ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት በለጠ በዘንድሮ የገና በዓል በዋናው ቄራ 2,953 የዳልጋ ከብት እንዲሁም 2,431 ትናንሽ እንስሳት/ በግ እና ፍየል/ በአጠቃላይ 5,384 እንስሳት እርድ እንደተከናወነ ገልፀዋል፡፡
ለእርድ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች የምንሰጠውን የእንስሳት እርድ አገልግሎት በተፈለገው ሰዓት፣የስራ ጥራትና ፍጥነት ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም ሁሉም ደንበኞች ደስተኛ መሆናቸውን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በአቃቂ ቅርንጫፍ ቄራ 553 የዳልጋ ከብት እንዲሁም 49 ትናንሽ እንስሳት/ በግ እና ፍየል/ የእንስሳት እርድ መከናወኑም ተገልጿዋል፡፡
በዋናው እና በቅርንጫፍ ቄራው በጥቅሉ 5,986 የእንስሳት እርድ የተከናወነ ሲሆን አንደአጠቃላይ የበዓል ስራው መልካም አፈፃፀም የተመዘገበበት እና ያለምንም የደንበኞች ቅሬታ የተጠናቀቀ መሆኑ ይበልጥ የሚያተጋ የሞራል ስንቅ ያደርገዋል ሲሉ ሃላፊዋ አብራርተዋል፡፡
ታኀሣሥ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
