በመጨረሻም ጆ ባይደን የጋዛዉ ጦርነት በቃ አሉ

የእስራኤልና ሀማስ ተኩስ አቁም ስምምነት በሰዓታት ዉስጥ ይፈፀማል ተብሏል፡፡

በእስራኤልና በሀማስ መካከል ታጋቾችን ለመልቀቅ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በዶሃ ሲካሄድ የቆየው ውይይት ለፍፃሜ መቃረቡ ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስምምነቱ ፍሬ ሊያፈራ ተቃርቧል ብለዋል፡፡

ስምምነቱ እውን ሆኖ ወደ ተግባር መለወጥ ከተቻለ በ42 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

እስራኤል ወታደሮቿን በርካታ ፍልስጤማውያን ካሉበት ስታስወጣ ሀማስ በምትኩ ታጋቾችን ይለቃል።

የእስራኤልና ሀማስ ጦርነት እስካሁን 46ሺ 584 ፍልስጤማውያን ሲሞቱ 109ሺ 7 መቶ 31 ቆስለዋል።

ከነጩ ቤተመንግስት ሊወጡ አምስት ቀናት ያላቸዉ ጆ ባይደን የተኩስ አቁሙን እዉን ለማድረግ በሙሉ አቅማቸዉ እየሰሩ ነዉ፡፡

ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸዉ ሁኔታዎች መስመር ካልያዙ አደጋ ነዉ ብለዋል፡፡

አባቱ መረቀ

ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *