ላለፉት አምስት ወራት 1መቶ 93ሺ ዮኒት ደም ለመሰብሰብ እቅድ ተይዞ 1 መቶ 79 ሺህ ዮኒት ደም መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል ።
የኢትዮጵያ ደም እና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት 92 በመቶ ከእቅዱ ማሳካት ተችሏል ።
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ወደ 46ሺህ ዮኒት ደም መሰብሰቡን ተናግረዋል።
ከሌላው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀርም አፈፃፀሙ መሻሻሎች አሳይቷል ብለዋል ።
የፀጥታ ችግር ያለባቸው የተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች ላይ ደም ለመሰብሰብ እንደሚቸገሩም ነግረውናል።
የደም ህክምናን የሚፈልጉ ታካሚዎች ቁጥር ከፍ ያለበት ሁኔታ በመኖሩ አሁንም የደም ለጋሹ ቁጥር እየጨመረ መምጣት እንዳለበት ገልፀዋል።
ሐመረ ፍሬው
ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም
