የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ  ዮሴፍ ገብረወልድን  አድርጎ ሾመ!

አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ከተማ ሴቶች ቡድን እንዲሁም ያለፉትን ሦሰት ዓመታት የአርባምንጭ ከተማ ሴቶች ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ባለፈው ዓመት በጋና አክራ የአፍሪካ ጨዋታዎች ላይም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።

  አሰልጣኙ   ብሔራዊ ቡድንን ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ለማሰልጠን ተስማምተዋል። የአርባምንጭ ከተማ ኃላፊነታቸውን በመልቀቅ ሙሉ ለሙሉ ትኩረታቸውን ብሔራዊ ቡድኑ ላይ ለማድረግም ተስማምተዋል።

አሰልጣኝ ዮሴፍ ከአንድ ወር በኋላ በ2026 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ዩጋንዳን የሚገጥመውን ቡድን በማዘጋጀት የብሔራዊ ቡድን ሥራቸውን ይጀምራሉ።

ጋዲሳ መገርሳ

ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *