ህንፃዎች ስር የሚገኙ መኪና ማቆሚያዎች ለታለመላቸው አላማ እያገለገሉ ባለመሆኑ የመኪና ማቆሚያ ችግር መኖሩ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የህግ ድጋፍ አግኝቶ የህንፃ ስር መኪና ማቆሚያዎችን እንዲሁም የመንገድ መኪና ማቆሚያዎችን ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ለማድረግ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ነገርግን አሁንም የህንፃ ስር መኪና ማቆሚያዎች ለታለመላቸው አላማ እየዋሉ ባለመሆናቸው ህብረተሰቡ መኪና ማቆሚያ እየተቸገረ መሆኑን ሰምተናል።

በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የፓርኪንግ እና የመንገድ ትራፊክ መሠረተ ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጌታቸው ቂርቆስ፣ ልደታ እና ቦሌ ክፍለከተሞች ከፍተኛ የህንፃ ቁጥር ከሚገኙባቸው አከባቢዎች መካከል መሆናቸውን አንስተዋል።

በእነዚህ ክፍለከተሞች ባለስልጣኑ ህንፃዎችን የመፈተሽ ስራ እየሠራ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

የባለስልጣኑ ባለሙያ ከህንፃው ባለቤት ወይም ከአስተዳደሩ ጋር በመሆን ህንፃውን የመፈተሽ ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በህንፃው የሚስተካከል ነገር ካለ አጭር ቀጠሮ እንደሚሰጥ እና በተሰጠው ጊዜ የማይስተካከል ከሆነ ወደ ቅጣት ከፍ ሲልም ጉዳዩ ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት እንደሚተላለፍ ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

አፎሚያ አሸናፊ

ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *