በጦርነቱ ምክንያት 80 በመቶ የሚሆነዉ የጋዛ ክፍል መዉደሙን የፍልስጤም ባለስልጣን አስታዉቀዋል፡፡
በዚህም 3 መቶ ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ቤት አልባ መሆናቸዉ ነዉ የተነገረ ነዉ፡፡
በተለይም በሰሜናዊ ጋዛ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ቄያቸዉ ወድሟል ተብሏል፡፡
ጋዛ በ15 ወራት ዉስጥ 80 በመቶ ስትወድም መልሶ ለመገንባት ግን 15 ዓመታት እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ያመለክታል፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ ዕርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎች እየገቡ መሆናቸዉን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
አባቱ መረቀ
ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም
