“በኢትዮጵያ አሁን ላይ ሁሉንም ጉዳዮች  በውይይት እንፍታ የሚል መሪ እና መንግሰት ነው ያለው”  የመንግሰት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር )

በብሔራዊ መግባባት ላይ ያተኮረው ሁለተኛው የፓርላማ የዜጎች መድረክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ ውይይትም በተለየ በሃገራዊ መግባባት እና በሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዙሪያ ብዙ ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች እየተነሱ ይገኛል፡፡

የመንግስትን መሪ አቋምን  በተመለከተ በውይይቱ  ተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቷል፡፡

አሁን ላይ የመንግስት አቋምን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የመንግሰት ተጠሪ  ተስፋዬ በልጅጌ( ዶ/ር) ፤ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ”ሁሉንም አጀንዳዎች በውይይት እንፍታ የሚል  መንግስት ነው” ያለው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ዶ/ር  ተስፋዬ በተለይም ሁሉንም የፖለቲካ አጀንዳዎች በውይይት እና በጠረጴዛ  ዙሪያ እንፍታ የሚል የመነግስት ተቋም ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

ለአብነት ያነሱት  ሃገራዊ ምክክር  ምክር ቤት መቋቋሙ የመንግስት ቁርጠኝነትን በደንብ ያሳየ መሆኑን አመላካች ነው ሲሉ ገለጸዋል፡፡

የመንግሰት ተጠሪው ለዚህ ማሳይ ብለው የቤንሻነጉል ጉምዝ  ታጣቂዎች ሰላም አማራጭን መከተልን እንዲሁም የቅርቡን የእነ ጃል ሰኚ እና የመንግሰት የሰላም ስምምነትን ጠቅሰዋል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *