የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ህገወጥ የነዳጅ ግብይት እየተባባሰ መምጣቱን አስታውቋል።
የቢሮዉ የኢንስፔክሽና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸዉ ቆጲሳ፤ባለፉት ስድስት ወር ብቻ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 325 ሺህ 108 ሊትር ነዳጅ መያዙን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በገንዘብ ሲሰላ 29 ሚሊዮን 422 ሺህ 274 ብር መሆኑን አቶ ጌታቸው ነግረውናል።
ዳይሬክተሩ የነዳጅ ምርት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ መምጣቱንም ጠቁመዋል።
በደቡብ ክልል ከተሞች የኩፖን ሥርዓት በመዘርጋቱ ሥርጭት ላይ ያለውን የቤንዚን ምርት በአግባቡ ማሰራጨት መቻሉንና ለክትትልም ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ያነሱት አቶ ጌታቸው በኦሮሚያ ክልልም እንዴት ይሁን የሚለው ጥናቱ ተጠንቶ ማለቁን አስረድተዋል።
ጥናቱ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ሁሉም ማህበረሰብ ጋር መድረስ ያስችላል ብለዋል።
ልኡል ወልዴ
ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም
