የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ጥለዋል።
ትራምፕ “በአሜሪካ እና የቅርብ አጋሯ እስራኤል ላይ ቅቡለነት እና መሠረት የሌለው ተግባር እየፈጸመ ነው” ሲሉ የከሰሱት ዓለም አቀፉ የጦር የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ላይ ማዕቀብ የጣሉበት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ላይ ፈርመዋል።
ትራምፕ አይሲሲ ላይ የጣሉት ዕቀባ እና ቪዛን የሚያጠቃልል ነው።
የቪዛ ዕቀባው የአሜሪካ ወይም የአጋሯቿ ዜጎች ላይ ምርመራ የሚያደረጉትንና የሚረዱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻችን ዒላማ ያደረገ ነው።
ታራምፕ ይህንን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የፈረሙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ዋሽንግተንን እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው።
ባለፈው ጥቅምት ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ኔታኒያሁ በጋዛ ፈጽመውታል ባለው የጦር ወንጀል ምክንያት የእስር ትዕዛዝ አውጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ይህንን ክስ እስራኤል አትቀበለውም። በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ የሐማስ የጦር አዛዥ ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል።
አሜሪካ የዚህ ዓለም አቀፍ ተቋም አባል አይደለችም። በተደጋጋሚም በአሜሪካ ዜጎች ላይ በፍርድ ቤቱ የሚተላለፍ ውሳኔዎችን ውድቅ አድርጋለች።
አይሲሲ እስራኤል ራሷን የመካለከል መብቷ ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ኢራን እና ጸረ እስራኤል የሆኑ በድኖችን ችላ ብሏል ሲል ዋይት ኃውስ ገልጿል።
ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካ በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል ፈጽማ እደሆነ ምርመራ ሲያደረጉ የነበሩ የአይሲሲ ባለስለጣናት ላይ ማዕቀብ ጥለው ነበር። ሆኖም ማዕቀቦቹ በተኳቸው ጆ ባይደን ተሽረዋል።
ባለፈው ወር የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አይሲሲ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ድምጽ ሰጥቷል። ሆኖም ረቂቁ ላይ የሕገ መወሰኛው ምክር ቤት ሳይስማማበት ውድቅ ሆኗል።
ሐሙስ ጥር 29/2017 የተሰራጨ የዋይት ኃውስ የውስጥ መልዕክት (ሜሞ) ሄግ የሚገኘውን ዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት “አሳፋሪ የሆነ የሞራል እኩልነት” በሐማስና እስራኤል መካከል በመፍጠር በተመሳሳይ ጊዜ የእስር ትዕዛዝ አውጥቷል ሲል ይከሳል።
ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም
