የህወሓት አመራሮች ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የስነምግባር መመሪያ ተፈራረሙ

የህወሓት አመራሮች ሁሉን አቀፍ ችግሮቻቸውን በሰላምና በውይይት ለመፍታት ተስማምተዋል፤ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የስነ ምግባር ደንብ አውጥተው ተፈራርመዋል ሲሉ የትግራይ የሀይማኖት አባቶች አስታወቁ።

የሀይማኖት አባቶቹ ዛሬ በመቀለ ከተማ በሰጡት መግለጫ፤ “ስምምነቱን ወደፊት ለማራመድ በሚል ሁለቱም ወገኖች የስነ ምግባር ደንብ አውጥተው ተፈራርመዋል” ማለታቸውን ትግራይ ቴሌቪዢን ዘግቧል፡፡

መመሪያዎቹ ምን ላይ እንዳተኮሩ ግን መረጃው የገለጸው ነገር የለም።

ላለፉት ሁለት ወራት መሪዎቹ ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ በተናጠልም ይሁን በጋራ በተደጋጋሚ ጥረት ስናደርግ ነበር ሲሉ የገለጹት የክልሉ ምስራቃዊ ዞን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ሁሉንም ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

ከወራት በፊት የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ሁለቱን የህወሓት ቡድን በማቀረራብ “ችግሮቻቸውን በመመካከር ለመፍታት ቃል እንዲገቡ ባቀረብነው ጥያቄ ላይ አዎንታዊ ምላሽ አግኝተናል” ሲሉ መግለጻቸው መዘገቡ ይታወሳል።

የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *