ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን “አምባገነን” ብለው መጥራታቸው የሁለቱን መሪዎች መቃቃር ይበልጥ አባብሶታል።
ትራምፕ ይህንን ያሉት ዜሌንስኪ ኪየቭ የተገለለችበት እና በሳዑዲ አረቢያ ለተደረገው በአሜሪካ እና ሩሲያ ንግግር በሰጡት ምላሽ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በሚተዳደረው በሞስኮ “የሐሰት መረጃ ላይ ነው” በማለት ከወቀሱ በኋላ ነው።
ፍሎሪዳ ውስጥ በሳዑዲ በሚደገፈው የኢንቨስትመንት ስብሰባ ላይ ትራምፕ እንደተናገሩት ዜሌንስኪ “በጣም ጥሩ የነበሩበት ብቸኛው ነገር ጆ ባይደንን በከንቱ ማታለል ላይ ነው” ብለዋል።
ትራምፕ ‘በትሩዝ ሶሻል’ ልጥፍ ላይ ተመሳሳይ ቃል ከተጠቀሙ ጥቂት ሰዓታት በኋላ በፍሎሪዳ ሲናገሩ ዜለንስኪን “አምባገነን” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።
“ምርጫ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም። በዩክሬን ብዙም አይፈለገም። እያንዳንዱ ከተማ እየፈረሰ እንዴት ከፍ ሊል ይችላል?” ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።
የዘለንስኪን መንግሥት “ስምምነቱን አፍርሷል” ሲሉ በመክሰስ ከዩክሬን የከበሩ ማዕድናት ለማግኘቱ ያደረጉትንም ሙከራ ጠቅሰዋል።
ትራምፕ ዘለንስኪ “መጥፎ ሥራ ሠርቷል፣ አገሩ ፈርሳለች፣ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያለምክንያት ሞተዋል” ሲሉ “የትሩዝ ሶሻል” ልጥፋቸውን አስተጋብተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ “ጦርነቱን በተሳካ ሁኔታ ለማቆም ከሩሲያ ጋር ድርድር እያደረገች ነው” ብለዋል።
የዋይት ሀውስ ባለስልጣን የትራምፕ ልጥፍ ለዘለንስኪ ለሰጡት የ”ሃሰት መረጃ” አስተያየቶች ቀጥተኛ ምላሽ ነው ብለዋል።
ማክሰኞ የአሜሪካ እና የሩሲያ ባለስልጣናት ከሩሲያ የዩክሬን ወረራ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ፊት ለፊት ተገናኝተው ንግግሮችን አድርገዋል።
የዩክሬን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አርሴኒ ያሴንዩክ የትራምፕን አስተያየት ተከትሎ ሩስያ “አሁን ፈንጠዝያ ላይ ነች” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
“ቮልዲሚር ዘለንስኪ ሕጋዊ ፕሬዚዳንት ናቸው” ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር “በወታደራዊ ሕግ ስር ምርጫ ማካሄድ አንችልም” ብለዋል።
የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
