በናይል ወንዝ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ስርዓት እንዲሰፍን ሁሉም የቡኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠይቋል።
ይህ የተባለው 19ኛው የሪጅናል ናይል ቀን የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት በሳይንስ ሙዚየም እየተከበረ ባለበት ወቅት ነው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በጉባዬው የተገኙ ሲሆን፤ “የአባይ ትብብርን ማጎልበት፣የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ለጋራ ልማት “በሚል መርህ ይከበራል ብለዋል።
ሚስትሩ በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያ ለዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ አጠቃቅምና ቀጣናዊ የጋራ ልማት መረጋገጥ የማይናወጥ አቋም አላትም ብለዋል።
የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን መቋቋም ለአባል ሀገራት የጋራ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽኑ የተፋሰሱ ሀገራት የልማት ትብብር በህግና ስርዓት እንዲመራ ከማድረጉ በተጨማሪ ለጋራ ጥቅም የሚውሉ ግድቦችን ለመስራት ያስችላል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም ስርዓት እንዲሰፍንና በናይል ሀገራት መካከከል ትብብርን ማዕከል ያደረገ ግንኙነት እንዲፈጠር ጥረት አድርጋለች አሁንም ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፍሎሬንስ አዶንጎ፤ የመሰባሰባችን ዋነኛው አላማችን የተፋሰሱን ሀገራት የልማት ትብብር ማጠናከር ነው ብለዋል፡፡
በጉባዔው የተፋሰሱ ሀገራት እና ትብብር ያደረጉ ሁሉ በጋራ ለማደግ ያላቸውን ፍላጎት የሚያመላክት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ሌሎችም ቆም ብለው የመተባበር እና ያለመተባበር የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ማገናዘብ ተገቢ ነው፤ተነጣጥለን ረዥም መጓዝ አይቻልም ብለዋል።
የናይል ቀን በየዓመቱ ፌቡራሪ 22 በተፋሰሱ ሀገራት ይከበራል፡፡
የናይል ተፋሰስ ኮሚሽን በተፋሰሱ አባል ሀገራት ስምምነት መሰረት በቅርቡ እውን ይሆናል መባሉን ሰምተናል፡፡
ልኡል ወልዴ
የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
