ተመድ በሱዳን ያለው ጦርነት መባባስ በሀገሪቱ መጠነ ሰፊ ረሀብ እንዲታይ እያደረገ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

በሀገሪቱ 24.6 ሚሊየን ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብ ተዳርገዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተናግሯል።

የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ በሱዳን በሁለቱ የጦር ሀይሎች መካከል ለሁለት ዓመታት የተጠጋዉ ግጭት ሀገሪቷን ወደ  ገሀነም ቀይሮታል ሲል ነዉ የገለፀዉ ።

ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶች እየታዩ ቢሆንም የእርዳታ ድርጅቶች በጦርነቱ ሳቢያ ስራቸዉን ስለማቋማቸዉ ጠቅሷል።

ከሰሞኑ  ከግማሽ ሚሊዩን በላይ  የተፈናቃይ ቁጥር ባለዉ የዘምዘም ካምኘ እርዳታ እየሰጠ የነበረዉ የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በግጭቱ መባባስ ምክንያት በካምፑ እየሰጠ የነበረዉ እርዳታ ለማቆም መገደዱን አሳዉቋል።

የሱዳንን ድንበር ጥሰው የተሰደዱትን 3.4 ሚሊዮን ጨምሮ ከ12 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉን ሪፓርቱ ጠቁሟል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት እና ፆታዊ ጥቃት  የደረሰባቸው ህጻናት ከመደበኛ ትምህርት አቋርጠዋል ብሏል።

በተጨማሪም የዓለም ምግብ ፕሮግራም በካምፑ  የምግብ እርዳታ መቋረጡን በጸጥታ ሁኔታ  ምክንያት እንደሆነ  ማረጋገጡን ተገልፆል።

የፀጥታው ምክር ቤት ሁሉም ተዋናዮች በአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋት እንዲያከብሩ እየጠየቀ ቢገኝም  የጦር ወንጀል  ግድያዎችን ስለመኖራቸዉ  ሪፖርቶች አረጋግጠዋል ብሏል።

የሱዳኑ አምባሳደር አል ሀሪዝ ኢድሪስ መንግስታቸው ሰብዓዊ ርዳታዎችን ለማመቻቸት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠው ሀገሪቱ የወደፊት ፖለቲካዋን ለመፍታት እየሰራች  መሆኑን እየገለፁ ይገኛል ሲል አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል።

ቁምነገር አየለ

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *