ኩባንያዉ ለወደቁትን አንሱ የነዳያን በጎ አድራጎት ማህበር በየካቲት ወር ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታዉቋል፡፡
በየካቲት ወር የኩባንያዉን ማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች ብዛት ልክ 30 ብር እንደሚለግስ ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ሼር በሚደረጉ ልጥፎች ብዛት ደግሞ 10 ብር ለበጎ አድራጎት ማህበሩ የሚለግስ መሆኑን አስታዉቋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በጥር ወር ለካለን ብናካፍል የሕፃናት፣ አረጋዊያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ድርጅት ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ፡፡
በየወሩ ከሚደረጉት ድጋፎች በተጨማሪ በቴሌብር ለበጎ አድራጎት በሚለው አማራጭ የፈቀዱትን የገንዘብ መጠን መለገስ የሚቻል መሆኑንም ኩባንያዉ አስታዉቋል፡፡
ኩባንያዉ ባለፈዉ ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ ለመቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
እስከዳር ግርማ
የካትት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
