የጋቦኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ብሪስ ኦሊጊ ንጌማ በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።
ንጉሜ እ.ኤ.አ. በ2023 የቦንጎን የ55 ዓመታት የቤተሰብ አገዛዝ ባቆመው መፈንቅለ መንግስት ስልጣኑን የተቆጣጠሩት፡፡
አሊ ቦንጎ ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው በታወጀ ከደቂቃዎች በኃላ ነበር በጄኔራል ብሪስ ኦሊጊ ንጌማ የተመሩት ወታደራዊ መኮንኖች መንበረ ስልጣኑን የነጠቋቸው፡፡
በወቅቱም ያለፉ ምርጫዎችን ስህተት ላለመድገም ለምርጫ መጣደፍ እንደማያስፈልግ ሲሉም ተደምጠው ነበር ወታደራዊ መሪው፡፡
ይሁን እንጂ ሀገሪቱ አዲስ ህገ መንግስት እና የምርጫ ህግ ማውጣቷ ተከትሉ ንጉሜያ አሁን በምርጫው ብሳተፍ እወዳለሁ ማለታቸው ተሰምቷል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ንጌማ ሰኞ ዕለት ለጋቦናውያን እና ደጋፊዎቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሚያዚያ 12 በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር የወሰኑት “በጥንቃቄ በማሰላሰል እና ለብዙ ወሳኝ የሀገሪቱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት” ነው ።
‹‹ሃገር ለማነጽ ተነስቼያለሁ፡፡ ይህችን ሃገር ለመገንባት ድጋፋችሁ ያሻኛል፡፡ ከጎኔ ቆማችሁ እንድታበረቱኝ እጠይቃለሁ›› ሲሉ ከሰሞኑ 50ኛ ዓመታቸውን የያዙት የመፈንቅለ መንግስት መሪ ተናግረዋል፡፡
መግለጫው የተሰማው የሃገሪቱን ቀዳሚ የስልጣን ወንበር የመቆናጠጥ ፍላጎት እንዳላቸው ለወራት ሲናፈስ ከቆየ በኋላ ነው፡፡
ጋቦን የነዳጅ ዘይት ሃብት እና ሰፊ ደኖች ቢኖራትም ከ2.4 ሚሊዮን ህዝቦቿ አንድ ሶስተኛው ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖሩ የመንግስታቱ ድርጅት ገልጿል።
የካትት 25 ቀን 2017 ዓ.ም
