አሜሪካ ጦርነት ከሆነ ፍላጎቷ ለማንኛውም ጦርነት ዝግጁ ነኝ ብላለች ቻይና።
ቻይና በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየጨመረ የመጣውን የንግድ ታሪፍ ጭማሪ አጥብቃ የተቃወመች ሲሆን ቻይና ማንኛውንም አይነት ጦርነት ለመዋጋት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።
ጦርነት አሜሪካ የምትፈልግ ከሆነ፣ የንግድ ጦርነት ወይም ሌላ ዓይነት ጦርነት ከሆነም እስከ መጨረሻው ለመዋጋት ዝግጁ ነኝ ሲል የቻይና ኤምባሲ በድጋሚ መግለጫ አውጥቷል።
ይህ የቻይና መግለጫ ቻይና እስካሁን በዚህ ጉዳይ ላይ ካሳየችው ጠንካራ አቋም ከባዱ መሆኑ ተነስቷል።
አሜሪካ በበኩሏ በተመሳሳይ የቻይንን አቋም በማንፀባረቅ ፤አሜሪካም ለየትኛውም ጦርነት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የውልሰው ገዝሙ
የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
