በ76 ማደያዎች ውስጥ ቁጥጥር ማድረጉን እና 40 በመቶ የሚሆኑት ከደረጃ በታች መሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕጋዊ ሥነ ልክና የቴክኒክ ደንብ ማስተባበር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ወለል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የቁጥጥር ስራው የተሰራው ውክልና ከተሰጠው ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡
ጣቢያችን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባገኘው ሌላ መረጃም የታሸጉ ምርቶች መጠናቸው እና በማሸጊያውቸው ላይ የተገለፀው ሁኔታ በትክክል የተሟላ እና በማሸጊያቸው ላይ ከተገለፀው ጋር የሚስማማ ትክክለኛ መጠን ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
በዚህም መሰረት 20 የምርት አይነቶች ላይ ቁጥጥር መደረጉን እና 6 የሚሆኑ የታሸጉ ምርት አምራች ድርጅቶች የተቀመጠውን የደረጃ መስፈርት ሳያሟሉ በመቅረታቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል፡፡
እርምጃ ከተወሰደባቸው የምርት አይነቶች ውስጥ የሲሚንቶ፣ የፓስታ እና ሞኮሮኒ ፤የዱቄት፣የሳሙና እንዲሁም የጨው ምርቶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡
ከምድር ሚዛን ጋር በተገናኘም 210 የሚሆኑ የመለኪያ መሳርያዎች ላይ ቁጥጥር እንደተደረገ እና 24ቱ ላይ ጉድለት እንደተገኘባቸው ጠቅሰዋል፡፡
ጉድለት ከተገኘባቸው መካከል አስራ ስምንቱ አስተካክለው ወደ ስራ የተመለሱ ሲሆን የተቀሩት ስድስቱ ግን ስራ እንዳይሰራባቸው መደረጉን መሪ ስራ አስፈፃሚው ገለፀዋል፡፡
ሐመረ ፍሬው
የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
