ክልሎች መክፈል ለማይችሉ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ድጎማ እንዲያደርጉ በህግ እንደሚገደዱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ ወርቁ፤ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የጤና መድህን ክፍያ መክፈል ለማይችሉት ድጎማ እንዲያደርጉ በህግ መስፈሩን ነግረውናል።

ጤና መድህን የመደጓጓመ ስርዓት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ፤ለጤና መድህን አገልግሎት የሚከፈለው ክፍያ፤ማንኛውም ከፍሎ መታከም የማይችሉ ሰዎች እንዲታከሙበት የሚደረግበት ነው ብለውናል።

ከዚህ ባለፈ ከጤና መድህ በሚገኘው ገቢ እና መንግስት በሚደጉመው 25 በመቶ ለህብረተሰቡ አግልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለጤና ተቋማት የህክምና መስጫ መሳሪያዎችን እና ሌሎች መድሃኒቶችን ለመግዛት እንደሚውል አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከተጀመረ 13 ዓመት እንዳለፉት የገለፁት አቶ ተስፋዬ፤በ2016 ዓ.ም መገባደጃ ላይ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች መጠን ከ54 ሚሊዮን ተሻግሯል ነው ያሉት።

ከዚህ ጥቁር ውስጥ 12 ሚሊዮን የሚጠጉት አባወራዎችና እማወራዎች በመንግስት እና በክልል አስተዳደሮች ተደጉሞላቸው የሚታከሙ መሆናቸው ነግረውናል ፡፡

የጤና መድህን የተጠቃሚው ቁጥር እና የሚገኘው ገቢ በፍጥነት እየጨመረ ስለ መምጣቱም ሰምተናል።

ልኡል ወልዴ

የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *