ሱዳን ለዓለም ዓቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ ክስ አቅርባለች፡፡
ድርጅቱ አስቸኳይ እርምጃዎች እንዲወስድ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ድጋፍ በምዕራብ ዳርፉር የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቃለች ሲል ፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የቀረበባትን ክስ ባፋጣኝ ውድቅ እንዲሆን ትጠይቃለች ሲሉ የኤምሬትስ ባለስልጣን ለሮይተርስ በላኩት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ክሱ “ምንም አይነት ህጋዊ ወይም ተጨባጭ መሰረት የለውም” ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግስትን ወክለው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ባለስልጣን፤ በምዕራብ ዳርፉር በሚገኘው የማሳሊት ጎሳ ላይ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች እና አጋር ሚሊሻዎች ከፈጸሙት ጥቃት ጋር በተያያዘ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዘር ማጥፋት ስምምነት የተጣለባትን ግዴታ ጥሳለች በሚል ክሱ መከፈቱን አንስተዋል፡፡
ሱዳን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተቀናቃኙን የሱዳን ፓራሚሊታሪ ቡድንን በማስታጠቅ አሰቃቂ የመብት ጥሰቶችን፣ ግድያን፣ ማሰቃየትን እና በሴቶች ላይ በሚሊሻዎች ጭምር መደፈር እንዲፈጸም አድርጋለች ስትል ከሳለች፡፡
ይህ ጥቃት የሱዳን አረብ ባልሆኑ ማሳሊት ጎሳዎች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጽዳት ዘመቻ አካል ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎችም በሪፖርቱ አስታዉቋል፡፡
የሱዳን ታጣቂ ሃይሎች ሀገሪቱን ካወደመ እና ብዙ የጎሳ ግድያዎችን ከፈጠረው ከRSF ጋር ለሁለት አመት የሚጠጋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መሆናቸዉን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
