እናት ባንክ ለአንድ ወር የሚቆይ በዋጋ ቅናሽ የህክምና አገልግሎት አዘጋጅቻለሁ አለ።

በ ‹‹እናት ጤና››የቁጠባ ሒሳብ የከፈቱ ደንበኞች የዘንድሮው የሴቶች ቀን ከሚከበርበት የካቲት 29 ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በልዩ የዋጋ ቅናሽ በተለያዩ የህክምና ማዕከላት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

በዋሽንግተን የሕክምና ማዕከል፣ በስዊዝ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያ፤ በመቅረዝና በአዲስ ሕይወት ሆስፒታሎች በመገኘት የሕክምና አገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ባንኩ ለጤና እንክብካቤ ቁጠባ የማድረግ ዕቅድ ያላቸው እናቶችን፤ ግለ ሰቦችን፤ ቤተ ሰቦችንና ማኅበራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ፤ እናት ጤና የተሠኘ የቁጠባ ሒሳብ ማቅረቡንም አስታዉቋል፡፡

እናት ባንክ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ114ኛጊዜ፣ በአገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሴቶች ቀን (March 8) አስመልክቶ በአጋርነት አብረውት ከሚሠሩ የሕክምና ተቋማት ጋር በመተባበር፤ በልዩ የዋጋ ቅናሽ ለአንድ ወር የሚቆይ የሕክምና አገልግሎት ማዘጋጀቱን አስታውቋል ።

ሐመረ ፍሬው

የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *