6.5 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ተጓጉዞ ወደ ሀገር ገብቷል ተባለ።

ግብርና ሚኒስቴር ለ2017 እና 2018 የምርት ዘመን የሚያስፈልገውን 24 ሚሊዮን ኩምታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ መፈፀሙን እና ከዛም መካከል እስካሁን 6.5 የሚሆነውን ማስገባት መቻሉን አስታውቋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ከበደ ላቀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የገባውን አፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።

24 ሚሊዮን ኩምታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ለመፈፀም መንግስት 84 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎችም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ በመፈለግ ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ግዢ ከተፈፀመው ውስጥ መርከብ ላይ እንዲሁም ወደብ ላይ የደረሱ መኖራቸውንም ገልፀዋል ።

ሐመረ ፍሬው

የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *