የቀድሞዉ የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት በአደንዛዥ ዕጽ ግድያ ወንጀል መታሰራቸዉ ተገለጸ፡፡

የፊሊፒንስ ፖሊስ በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴሬትን በአደንዛዥ ዕጽ ወንጀል በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

የ79 አመቱ አዛውንት ከሆንግ ኮንግ ማኒላ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከ2016 እስከ 2022 የደቡብ ምስራቅ እስያዋ ሀገር ፕሬዝዳንት በነበሩበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት እና ከዚያ በፊት የዳቫኦ ከተማ ከንቲባ ሆነዉ ለፈጸሙት አረመኔያዊ ፀረ-አደንዛዥ ዕፅ እርምጃ ይቅርታ አለመጠየቃቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

አዛዉንቱ በአየር ማረፊያዉ ሲታሰሩም “ምን ወንጀል ነው የሰራሁት?” ብለዉ ነበር የጠየቁት፡፡

የፕሬዝዳንቱ የቀድሞዉ ቃል አቀባይ ፊሊፒንስ በ2019 ከዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባልነት መዉጣቷን ተከትሎ እስሩን ‹‹ህገወጥ›› ብለዉታል፡፡

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ከአባልነት ከመውጣቷ በፊት ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ እርምጃ የመዉሰድ ስልጣን እንዳለው የዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቀደም ሲል አሳዉቋል፡፡

በፊሊፒንስ የሚገኘዉ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ጥምረት እስሩ በአደንዛዥ እጽ ጦርነት ለሞቱት እና ለቤተሰቦቻቸው “ታሪካዊ ጊዜ” ነዉ ሲል ጠርቶታል፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *