የታይላንድ መንግስት የአፍሪካ አገራት ዜጎቻቸዉን ለማስወጣት በኤምባሲዎቻቸዉ በኩል ተወካይ እንዲልኩ ጠየቀ።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በማይናማር የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራችን ለመመለስ የግድ የኤምባሲ ተወካይ መጥቶ መጠየቅ እንዳለበት ተነግሮናል ብለዋል።

ነገርግን ጥሪ ከተደረገበት ቀን አንስቶ ምንም የኢትዮጵያ ኢምባስ ተወካይ ወደ ታይላንድ እንዳልመጣ ገልፀዋል።

ከማይናማር ወጥተዉ ታይላንድ ካምፕ ከነበሩት ኢትዮጵያዊያን መካከል 32ቱ ትናንት ወደ አገር መግባታቸዉን አንስተዉ፤ ትኬት መቁረጥ ለማይችሉት ግን እስካሁን ምንም ምላሽ አለመሠጠቱን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ማይናማር የሚገኙ የዉጭ ዜጎች በኤምባሲዎቻቸው በኩል መዉጣታቸዉንና ኢትዮጵያዉያን ብቻ መኖራቸዉን ገልፀዋል።

የታይላንድ መንግስት ያልተቀበላቸዉ 3መቶ የሚጠጉ ዜጎች ማይናማር ካምፕ ዉስጥ እንደሚገኙም አንስተዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *