አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊን ማሰናበታቸውን አስታወቁ፣ ቢሮው የጊዜያዊ አስተዳደሩን መዋቅር በማፍረስ ተጠምዷል ሲሉ ተችተዋል

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉን የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆኑትን ሌተናል ጄነራል ፍስሃ ኪዳኑን ከሃላፊነት ማንሳታቸውን ትላንት መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ አስታወቁ፤ “የቢሮው ሃላፊ ወገንተኝነታቸው የማን እንደሆነ በግልጽ አሳይተዋል” ሲል ተችተዋል።

የጸጥታ ቢሮው “የመንግስትን ትዕዛዝ ከማክበር ይልቅ የመንግስትን መዋቅር ማፍረስ ላይ ተጠምዷል፣ ይህንንም የህግ ማስከበር ስራ አስመስሎ እያቀረበ ይገኛል” ሲሉ ኮንነዋል፤ “የቢሮው ሃላፊ ወገንተኝነታቸው የማን እንደሆነ በግልጽ ያሳያል” ሲሉ ባወጡት መግለጫ ተችተዋል።

በሌላ ዜና በክልሉ ደቡብ ምስራቅ ዞን በምትገኘው አዲጉዶም ከተማ በጸጥታ ሀይሎች እና በከተማዋ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ተሿሚዎች በሚደግፉ ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት አምስት ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን መቀለ ኤፍኤም 104 ሬድዮ በዘገባው አስታውቋል፤ ከቆሰሉት መካከል ሁለቱ ወደ መቀለ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ጠቁሟል።

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *