በሱዳን የቀጠለው የመንግስት ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ጦርነት በዘምዘም መጠለያ ካምፕ አካባቢ መደረጉ አደገኛ እንደሆነ የመንግስታቱ ድርጅት ገልጿል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ፋራሃን ሃቅ፤ የሱዳን ጦር ዘምዘም የመጠለያ ካምፕ አከባቢ ከበባ ማድረጉ በህይወት ለመትረፍ እየታገሉ ያሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን ስቃይ እያባበሰ ነው ብለዋል፡፡
በረመዳን ወቅት በካምፑ ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉን እና የምግብ እጥረትም መከሰቱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በአካባቢው ያለው የእቃዎች ዋጋ መናር ሌላዉ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በመጠለያ ካምፑና በኤል ፋሸር ከተማ መሃል ያለው መስመር ላይ በታጣቂዎች የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ እንደቀጠለና ጉዳቶችም እየደረሱ ስለመሆናቸዉ ነዉ የተናገሩት፡፡
የአናዶሉ ዘገባ እንደሚያሳየው፤ እስካሁን በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከ 20 ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሚሊዮኖች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም
