ይህንን ቁጥር ወደ 12 በመቶ ለመቀነስ እቅድ መያዙንም ሰምተናል፡፡
የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር ደረጄ ድጉማ፤ በአገራችን የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
ጤና ሚኒስቴር የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ እና ጤና ለማሻሻል ለ16 ሆስፒታሎች የህክምና መሳሪያ ዕቃዎችን ርክክብ አካሂዷል፡፡
እነዚህም ቁሳቁሶች ለአምስት ክልሎች የሚበረከቱ ሲሆን፤ ክልሎቹም አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ ፣ ትግራይና አፋር ናቸው፡፡
1.1 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ቁሳቁሶች ለክልሎቹ ተበርክተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና 13ተኛው የዓለም የአፍ ጤና አጠባበቅ ቀን እየተከበረ ነዉ፡፡
ዕለቱ፤ ‹‹ጥርሳችን እንዳይበላሽ ከአሁኑ እንቦርሽ›› በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር የጥርስ ህክምና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
የጤና ሚኒስቴር እና የደም እና ቲሹ ባንክ የአፍ ጤና ምርመራ እንዲሁም የአፍ ጤና አጠባበቅ ትምህርት በመስጠት እና በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው፡፡
አፎሚያ አሸናፊ
መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም
