“ክቡር ዶ/ር ደሳለኝ ለጥያቄዎ ትንሽ ሚዛናዊ መሆን ነበረቦት እንደዚህ መንግስት ሃሳብን በነጻ እንዲገለጽ የሚጋብዝ የለም“ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የምክር ቤቱ አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አሁን ላይ መንግስት ያለመከሰስ መብትን ሳያነሳ የምክር ቤቱን አባል እያሰረ ነው ፡፡ ሃሳቡን በነጻነት የሚገልጽም ሰው ፡፡ የሰላ ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችም በእስር ላይ ይገኛሉ ፡፡
ያለ ምንም ፍትሕም ለ20 ወራት ያለ ፍርድ እየተገላቱ ነው ይህ ደግሞ አግባብ እና ልክ አይደልም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ እንዲሁም በትግራይ ጦርነቶች ላይ መንግስት ያልተገባ ሃይል እየተጠቀመ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አባል ዶ/ር ደሳለኝ ምላሽ ሲሰጡ ‹‹ በአሁኑ ሰዓት እንደዚህ መንግስት ሃሳብን በነጻ እንዲገለጽ የሚጋብዝ የለም ››ብለዋል፡፤
በተለይ የጋዜጠኞችን እስር አስምልከተው ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈለገውን የሚያወራ ጋዜጠኛ ለምን ታሰረ የሚል ትችት አግባብ አይደልም ብለዋል፡፡
በተለይም በሃሳቦ ሚዛነዊ ሆነው መንግስትን ሊተቹ ይገባ ነበርም ብለዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አባል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ማንም ተነስቶ በሃይል መንግስትን ልንካ ቢልም የማይቻል ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በዚህም መንግስት በምርጫ የተመረጠን መንግስት አንጥላለለን ሲሉ ዝም ብሎ አያያይም የማየትም ስልጣን የለውም ብለዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
