ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ 17ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደገቡ የሚነገርላቸውን የኔዘርላንድ ዝርያ ያላቸው ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ መግባት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ እነዚህ ከሶስ መቶ አመታት በፊት ከኔዘርላንድ ወደ ደቡብ አፍሪካ የገቡት ሰፋሪዎች የዘር መድሎ ሰለባዎች በመሆናቸው እድሉ እደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡
ይሄንን የትራምፕን ፍቃድ ተከትሎ ወደ 70 ሺ የሚጠጉ የኔዘርላንድ ሰፋሪ የሆኑ ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ በመሄድ ጥገኝነት እንደሚፈልጉ ማመልከታቸውን በአሜሪካ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ የንግድ ምክር ቤት ገልጹዋል፡፡
ተቁዋሙ እንደገለጸው በዌብሳይቱ በኩል በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደች ደቡብ አፍሪካውያን ወደ አሜሪካ ስለሚሄዱበት ሁኔታ ላይ መረጃዎችን ጠይቀውኛል ብሉዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከተመለሱ በኃላ የአሜሪካና ደቡብ አፍሪካ ግንኙነት በተለያዩ ጉዳዮች እየሻከረ መምጣቱን ያስነበበው ቢቢሲ ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም
