የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ጸሃፊ የሆኑት ሰርጂ ሾይጉ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ለመገናኘት ፒዮንግያንግ ገብተዋል ተብሏል ፡፡
ባለስልጣኑ ከኪም ጆንግ ኡን በተጨማሪ ሌሎችንም የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ከቅርብ አመታት ወዲህ የሩሲያና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት እጅግ እየተጠናከረ ነው።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ያለውን ጦርነት ለማገዝ ሰሜን ኮሪያ 4ሺ ወታደሮችን ወደ ሩሲያ መላኳ የሚታወስ ነው፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሬ ሩዴንኮ ወደ ሰሜን ኮሪያ በመጓዝ ከሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የሁለቱን ሃገራት ፖለቲካዊ ትብብር ከፍ ሊያደርጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገው እንደነበረ የሚታወስ ነው።
በቀጣይ ጉብኝቱ በመሪዎች ደረጃም ሊቀጥል እንደሚችል የዘገበው ሬውተርስ ነው።
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
