የሱዳን ብሄራዊ ጦር የ ፈጥኖደራሽ ሃይል ታጣቂዎችን በተሳካ ሁኔታ በዋና ከተማዋ ካርቱም ከሚገኘው የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ማስወጣት መቻሉን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል።
የፈጥኖደራሽ ሃይሉ ከሁለት አመታት በፊት የሱዳንን ጦር በማስለቀቅ የፕሬዝዳንቱን መቀመጫ በእጁ አስገብቶ መቆየቱ ተዘግቧል ፡፡
የሱዳን ወታደሮች እጅግ እልህ አስጨራሽ ጦርነት በማድረግ ቦታውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ፎቶዎችን በመነሳት በማህበራዊ ድረገጾች ላይ አጋተዋል፡፡
ስለሁኔታው ግን ከሱዳን ጦር ባለስልጣናትም ሆነ ከፈጥኖ ደራሹ ሃይሎች ሃላፊዎች እስካሁን የተባለ ነገር የለም ተብሏል ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታጣቂ ሃይሉ በርካታ ቦታዎችን እየለቀቀ እንደሆነ እየተሰማ ነው፡፡
ባለፉት ሁለት አመታት የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከ ሃያ ሺ በላይ ዜጎችን ህይወት ሲቀጥፍ ። 14 ሚሊየን ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት መረጃ ያመለክታል ሲል የዘገበው የአናዱሉ ነው፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
