የእንግሊዙ ግሪን ሞሽን አለም አቀፍ የመኪና ኪራይ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

የእንግሊዙ ግሪን ሞሽን አለም አቀፍ የመኪና ኪራይ ኩባንያ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ቢሮ በመክፈት በይፋ ስራ መጀመሩን  አስታውቋል

ዋና መስሪያ ቤቱን በለንደን ያደረገው ይህ የእንግሊዙ ግሪን ሞሽን አለም አቀፍ የመኪና ኪራይ ኩባንያ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ቢሮ ሲከፍት የሚፈለገውን መስፈርት አሟልቶ እና አለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እንደሆነ ተገልጿል ፡፡

አገልግሎቱንም በአለማችን በ80 ሀገሮች ውስጥ በሚገኙት 700 ቢሮዎቹ እየሰጠ እንደሚገኝ የግሪን ሞሽን ኢትዮዽያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

አቶ ብዙአየሁ አክለውም አዲስ አበባ አለም አቀፍ ከተማ እንደመሆኗ መጠን ይህ የመጀመሪያው አለም አቀፍ ኩባንያ ወደ ስራ በመግባቱ ከተማዋ እንግዶቿን በአግባቡ እንድታስተናግድ በብርቱ ያግዛታል ከዚህም ባለፈ ለሀገር የውጭ ምንዛሪ በማምጣት ረገድና የስራ እድል በመፍጠር ደረጃም ትልቅ እድል ይሰጣል ብለዋል፡፡

ይህ ግሪን ሞሽን የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ የከተማዋን ስም እና ደረጃ በጠበቀ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ከግሪን ሞሽን ኢትዮዽያ ጋር የውል ስምምነት አድርጓል።

አቤል እስጢፋኖስ

መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *