ዳማሪዮስ ፋሽንና ቴክኖሎጂ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ ተማሪዎችን አስተምሮ ስራ ለማስያዝ  ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ።

ዳማሪዮስ ፋሽን እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በፋሽን፣ ስነ-ዉበት እና ሜካፕ እንዲሁም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ወጣቶችን ለማስተማር መዘጋጀቱን አስታዉቋል፡፡

ተቋሙ ስራ አጥነትን ለመቅረፍ አስተምሮ ስራ በማስያዝ የበኩሉን ለመወጣት ዝግጅቱን አጠናቆ ተማሪዎችን ሊቀበል እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሴኪዩሪቲ ትምህርት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑንም አስታዉቋል፡፡

ድርጅቱ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የስራ ዕድልን ለሰልጣኞች እንደሚያመቻችም ነዉ የገለጸዉ፡፡

ከተለያዩ የቢዝነስ ትምህርት ቤቶች ጋር ስምምነት ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፤በቀጣይም ከአገር ዉስጥና ከዉጭ አገር ተቋማት ጋር ስምምነቶችን ለመፈፀም በሂደት ላይ እንደሆነም አስታዉቋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *