የደቡብ ኮሪያ ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት በሃገሪቱ ላይ የወታደራዊ አስተዳደር ህግ በማውጣት ክስ የቀረበባቸውን ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዬውል ቢሮዋቸውን እንዲለቁ ውሳኔ መስጠቱ ተገልጻል፡፡
ይሄም የፍርድቤቱ ውሳኔ በዋና ከተማዋ ሴኡል በሰውዬው ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ላይ ሁለት አይነት ስሜት ፈጥሩዋል ተብሉዋል፡፡
ፍርድቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በቀጣዮቹ ስልሳ ቀናት ውስጥ ለአዲስ ፕሬዝዳንት በሃገሪቱ ድምጽ እንዲሰጥ ትእዛዝ አስተላልፉዋል፡፡
በዚህም የዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ የሆኑት ሊ ጄ ሚዩንግ የማሸነፍ ቅድመ ግምት እንደተሰጣቸው የዘገበው ኤዢያን ኒውስ ነው ፡፡
ገነነ ብርሃኑ
መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም
