ሩሲያ የብሪክስ አባል ሀገራት በዩክሬን ጦርነት ላይ የያዙትን አቋም እንደምታደንቅ የሩሲያ የብሪክስ ተወካይ ተናገሩ

ተወካዩ ፓቬል ክኒያዜቭ በቫልዳይ የውይይት ክለብ ላይ ባደረጉት ንግግር አቋሙን “ሚዛናዊ” ሲሉ ገልፀውታል።

ቻይና እና ብራዚል በዩክሬን ዙሪያ ያደረጉትን ስምምነት እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራትና ህንድ ዓለም አቀፍ የሰላም ጥረቶች አካል የሆኑ እንቅስቃሴዎችን እንዳደረጉ አንስተዋል።

“ይህ ማለት አጋሮቻችን ለምሳሌ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አንነግራቸውም ማለት ነው” ብለዋል።

ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *