በቻይና የነርሲንግ ቤት በደረሰ የእሳት አደጋ 20 ሰዎች ሞቱ

በቻይና ሰሜን ምስራቅ በሚገኝ አንድ የአረጋውያን ማቆያ ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 20 ሰዎች መሞታቸውን የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

በሄቤይ ግዛት በቼንግዴ ከተማ እሳቱ የተነሳው ማክሰኞ ምሽት ላይ ነው፡፡እሳቱ ከተከሰተ በሁለት ሰአት ውስጥ ሊጠፋ ችሏል ተብሏል።

ከቃጠሎው የተረፉ 19 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ሲሉ ዘገባዎች አመልክተዋል።

የቃጠሎውን መንስኤ ባለስልጣናት እያጣሩ ሲሆን ቤቱን በሀላፊነት የሚቆጣጠር ሰው በቁጥጥር ስር ውሏል። ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች እንዳልተገኙ ቢቢሲ ዘግቧል ።

ቻይና የአረጋዊን ቁጥር በ2019 እና በ2024 መካከል በእጥፍ ጨምሯል።

እ.ኤ.አ. በ 2023 በቤጂንግ የግል ሆስፒታል በደረሰ የእሳት አደጋ 29 ሰዎች ( አብዛኛዎቹ አረጋዊን ናቸው) ከሞቱ በኃላ የተከሰተ ሌላኛው ከፍተኛ ሞት የተከሰተበት አደጋ ሆኗል፡፡

ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *