የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትራምፕና ኔታንያሁ የጋዛ ነዋሪዎችን ለማፈናቀል ማቀዳቸዉ ከዓለም አቀፍ ህግ ጋር የሚቃረን ነዉ ሲል ገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ የጋዛን ህዝብ ወደ ሌሎች አገራት ለማስፈር በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የታቀደዉ ሀሳብ የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ ነው ሲሉ ውድቅ ማድረጋቸው ተዘግቧል።

ፍልስጤማውያን ከእስራኤል መንግስት ጎን ለጎን በፍልስጤም ግዛት ውስጥ መኖር መቻል አለባቸው፤በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ሊያመጣ የሚችለው ብቸኛው መፍትሄ ይህ ነዉ ብለዋል፡፡

ስለሆነም ፍልስጤማውያንን በግዳጅ ማፈናቀል ከዓለም አቀፍ ህግ ጋር የሚጋጭ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በክልሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል በሚል በተደጋጋሚ ይነሳል ለዚህ ምን ምላሽ አሎት ተብለዉ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የተነሳላቸዉ ጉተሬዝ፤ በስፍራዉ ያለዉ ሁኔታ ስለቃሉ ከምንጨነቀዉ በላይ በጣም የከፋ እና አሰቃቂ ነዉ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የዘር ማጥፋት መፈጸሙን ለመወሰን ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አግባብ ያለው አካል መሆኑን ገልጸው ፤የዓለም አቀፉን የፍትህ ፍርድ ቤት ውሳኔ አከብራለሁ ብለዋል፡፡

ዋና ጸሀፊዉ በፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ የጋራ ቅጣት እንደሆነ በማንሳት፤ በምንም መንገድ ትክክል ሊሆን አይችልም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *