ባለፈው አመት በ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው ሶስት አሜሪካውያን ፍርዳቸውን በሀገራቸው እንዲከታተሉ መላካቸውን የኮንጎ መንግስት ገለጸ

ሶስቱ አሜሪካዊያኑ የኮንጎን መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ አድርገዋል ተብለው በሃገሪቱ የጦር ፍርድ ቤት ክሳቸው ሲታይ ቆይቶ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው የነበረ ሲሆን በኃላም ፍርዳቸው ወደ እድሜ ልክ ተቀይሮላቸዋል፡፡

አሁን ላይ ሶስቱ አሜሪካውያን ወደ ሃገራቸው የተላኩ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ ግለሰቦቹ በኛ የህግ ጥላ ስር ይገኛሉ ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘም አሜሪካ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ በመአድኑ ዘርፍ አብረው ለመስራት ስምምነቶች ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን አሜሪካ በኮንጎ የመአድን ዘርፍ ላይ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ እቅዱ እንዳላት ተሰምቱዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑ ባለስልጣን በ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሁለቱ ሃገራት በመአድናት ዘርፍ በምን መልኩ በጋራ ሊሰሩ እንደሚችሉ በዝርዝር መወያየታቸው ተሰምቱዋል፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በወረርሽኝ በሽታዎችና በእርስ በርስ ጦርነቶች በከፋ ችግር ውስጥ መገኘቱዋ በሁለቱ ሃገራት የጋራ ስራ ላይ ችግር ስጋት እንደሚሆን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

ገነነ ብርሃኑ

ሚያዚያ 01ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *