” መታጠቢያ ቤቶችን መልሰን በውኃ እናንበሸብሻለን ” አሉ ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ መታጠቢያ ቤቶች የሚደርሰው የውኃ ግፊት መጠን ላይ የተጣለውን ገደብ የሚያነሳ ትዕዛዝ ፈረሙ።

ትራምፕ ከዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ ” የአሜሪካ መታጠቢያ ቤቶችን መልሰን በውኃ እናንበሸብሻለን ” ብለዋል። ከረዥም ጊዜ አንስቶ ገደቡ ለትራምፕ የጎን ውጋት ሆኖባቸው ነበር።

ከአከባቢ አየር ጋር በተያያዘ እና ውኃ ለመቆጠብ ሲባል በቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አማካኝነት ተግባራዊ የሆነውን ይህን ገደብ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ሽረውት ነበር።

ይሁንና ልክ እንደ ኦባማ ዲሞክራት የነበሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መልሰው ገደቡ እንዲቀጥል አድርገው ነበር። አሁን ደግሞ ትራምፕ ይህን ትዕዛዝ ሽረዋል።

ትራምፕ ዕሮብ ዕለት ማስፈፀሚያ ትዕዛዙን ሲፈርሙ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “እኔን በሚመለከት ቆንጆ ፀጉሬን ለመንከባከብ በደንብ መታጠብ ደስ ይለኛል ” ሲሉ አፊዘዋል።

በእስካሁን ገደብ መሠረት ከአንድ መታጠቢያ ቤት የሚፈሰው የውኃ ግፊት በደቂቃ 10 ሊትር ውኃ ገደማ ነበር።

ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *