የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰርት ዝግጅቱ ተጠናቋል ተባለ፡፡

ሚያዚያ 18 ቅዳሜ ምሽት በጊዮን ሆቴል የሙዚቃ ስራዎቹን ከአዲስ ሙዚቃዎች ጋር በማካተት ከአድናቂዎቹ ጋር ለመገናኘት መሰናዶውን እንዳጠናቀቀ ተገልጿል፡፡

ድምፃዊዉ በሚሊኒየም አዳራሽ የነበረው የመጀመሪያ ኮንሰርቱ ስኬታማ የነበረ መሆኑ፤ቀጣዩን ኮንሰርት ለማዘጋጀት መነሻ እንደሆነዉ ተናግሯል፡፡

በኮንሰርቱም ከሙዚቀኛዉ ዉጭ የተለያዩ ወጣት ድምጻዊያን ስራዎቻቸዉን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል ከሚዘጋጀዉ ኮንሰርት በኋላ በሀዋሳ ግንቦት 2 እንዲሁም በድሬደዋ ግንቦት 23 ሌሎች ድምፃዊያንን በማካተት የኮንሰርት ቱር እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በኮንሰርቱ ላይ የድንገተኛ ክሊኒክን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች እንደሚኖሩም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ስልተ-ምቶችን ጨምሮ ሬጌና ፖፕ ስልቶችን ያካተተዉን ‹‹ልዑል›› ሲል የሰየመው የመጀመሪያ አልበሙን ባለፈዉ ዓመት ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል፡፡

አፎሚያ አሸናፊ

ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *