ህግና ስርዓትን ተከትለዉ በማይሰሩ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ።

በትናንትናው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር የበጀት አመቱን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ቀርቧል።

የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ፤ኤጀንሲዎች ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለዉን ችግር ለመቅረፍ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የስራና አሰሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለዉን ችግር ለመቅረፍ ህግና ስርአትን ተከትለዉ በማይስሩ ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ ዕርምጃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መዉሰድ እንዳለበት በዚሁ ወቅት ተጠይቋል።

ለውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውንም ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ተናግረዋል፡፡

ሁሉንም አካባቢዎች ታሳቢ ያደረገ ለዜጎች ፍትሃዊ የሆነ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ፤ ወደ ውጭ ሀገራት የሚሰማሩ ዜጎችም ሰብአዊ መብታቸውና ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲሰሩ ክትትል መደረግ እንዳለበትም ተገልጿል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *