ፍልስጤም በሰኔ ወር ፈረንሳይ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት ማቀዷን በደስታ ተቀብላለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ የፈረንሳይን እቅድ፤የሁለት መንግስታት መፍትሄን ለማስጠበቅ እና ሰላም ለማስፈን ትክክለኛ እርምጃ ነው ሲል ገልጾታል፡፡
የሐማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ማህሙድ ማርዳዊ፤ ውሳኔውን እንደሚቀበሉት ተናግረዉ፤ፈረንሳይ በፖለቲካዉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር እና የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እንደመሆኗ መጠን ወደ ፍትሃዊ መፍትሄዎች እንድንሄድ ተጽዕኖ በማሳደር፣ ወረራው እንዲቆም ግፊት በማድረግ የፍልስጤም ህዝቦችን ምኞት እውን ማድረግ ትችላለች ብለዋል፡፡
ይህን ተግባራዊ ማድረግ ከተቻለ በህዝባችን ህጋዊ ብሄራዊ መብቶች ዙሪያ ባለዉ ዓለም ዓቀፍ አቋም ላይ አዎንታዊ ለውጥ የሚያመጣ ወሳኝ እርምጃ ነው ብለን እንቆጥረዋለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአንፃሩ እስራኤል ለፍልስጤም መንግስት ሊሰጥ የሚችለውን ማንኛውንም እውቅና ነቅፋለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጌዲዮን ሳአር፤በ X ገጻቸዉ፤ልቦለድ ለሆነ የፍልስጤም መንግስት በማንኛዉም አገር የሚሰጥ የአንድ ወገን እውቅና ማለት ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ለሽብር ሽልማት እና ለሃማስ ማበረታቻ ይሆናል።
እነዚህ አይነት ድርጊቶችም በክልላችን ሰላምን፣ ደህንነትን እና መረጋጋትን የሚያመጡ ሳይሆኑ በተቃራኒው እነርሱን የበለጠ የሚያርቁ ናቸዉ ብለዋል፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ፓሪስ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት እቅድ ማውጣቷን እና ይህንንም እስከ ሰኔ ወር ድረስ ለማድረግ ማቀዷን አስታዉቀዋል፡፡
እስከዳር ግርማ
ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም
