በአዲስ አበባ በ2016 አመት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ401 ሰዎች ህይወት አልፏል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት የ2016 አመታዊ የትራፊክ አደጋ መረጃ ትንተና ዉጤትን ይፋ አድርጓል።

ዘጠነኛዉ አመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርት መረጃ እንደጠቆመዉ በአመቱ 401 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በዚህም ከፆታ አንፃር ከተከሰተዉ አጠቃላይ የሞት አደጋ ዉስጥ ከፍተኛዉ ቁጥር ወንዶች ላይ የደረሰ ነዉ ተብሏል።

በትራፊክ አደጋ ከሚከሰት ሞት 78 በመቶዉን ወንዶች ተጎጂ ሆነዋል ተብሏል።

ይፋ በተደረገዉ የመረጃ ትንተና መሠረት በመንገድ ትራፊክ አደጋ ህይወታቸዉን ያጡት እድሜያቸው ከ20 እስከ 39 የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸዉን አሳይቷል።

በባለፉት ዘጠኝ ተከታታይ አመታት የሞት አደጋ የደረሰባቸዉ እግረኞች ናቸዉ የተባለ ሲሆን መረጃዉ 86 በመቶ መሆኑን ገልፆል።

በተመዘገበዉ የሞት አደጋ ከሰአት አንፃር ከምሽት 12 እስከ 4 ሰአት ሰአት ባለ ልዩነት ዉስጥ እንደሆነ ተገልፆል።

ቅዳሜ ቀን አደጋዎች በስፋት የተስተዋለበት ነዉ ተብሏል።

በሞት አደጋዉ ካደረሱት ዉስጥ ከፍተኛዉ የአዉቶሞቢሎች ሲሆን ተሳፋሪ የጫኑ ሚኒባሶች እንዲሁም የጭነት ተሽከርካሪዎች ይገኙበታል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2016 የተመዘገበዉ አደጋ ከ2015 አመቱ ጋር ሲነፃፀር በ ሰባት ሰዎች ቀንሷል የተባለ ሲሆን ከባድ የአካል ጉዳትም እንዲሁ በሶስት በመቶ መቀነስ ችሏል ሲል ሪፖርቱ ጠቁሟል።

በከተማዋ ለሞት እና ለከባድ የአካል ጉዳት የሚያጋልጡ ቦታዎች መለየታቸዉን የተገለፀ ሲሆን የመንገድ ደህንነት የማሻሻያ እርምጃ ትኩረት እንዲያገኙ ያስችሏል ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *