የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 አንዱ ማስፈጸሚያ የሆነው አለም አቀፍ አትሌቶች እና የተለያዩ ክለቦች የሚሳተፉበት የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዚያ 19/2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል ።

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤የኢትዮጵያ ታምርት 10ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ዋና ዓላማ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ችግሮች ለመፍታት እና ለማሳደግ የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ማስተዋወቅ መሆኑ ተነግሯል።

እንዲሁም ገቢ ምርትን በመተካት የተሰማሩ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የስፖርት አልባሳት ማስተዋወቅ እና የማምረት አቅማቸውን ማሳየት አንደሆነም ተገልጿል።

የሩጫው መነሻ መስቀል አደባባይ ከ12፡30 ጀምሮ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ዉድድሩ ላይ ከ34 ክለቦች የተወጣጡ ከ 5መቶ65 በላይ አትሌቶች እና 80 ወንድ እና 35 ሴት የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከክልል፣ ከከተማ አስተዳደር እና በግል የሚወዳደሩ አትሌቶች እንደሚገኙበትም ተገልጿል።

ውድድሩን ለየት የሚያደርገው አንዱ ወደ ውጭ ሄደው መወዳደር ላልቻሉ አትሌቶች በሀገር ውስጥ እድል መፍጠሩ መሆኑ ተጠቅሷል።

ለውድድሩ አሸናፊዎች 1ኛ ለሚወጡ 300ሺ ብር ፣2ኛ ለሚወጡ 200ሺ ብር እና 3ኛ ለሚወጡ ደግሞ የ100ሺ ብር ሽልማት አዘጋጅቷል ተብሏል።

ሐመረ ፍሬው

ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *