በመዲናዋ  689 አሽከርካሪዎች ህይወት በማጥፋት እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ  እየተፈለጉ ይገኛሉ ተባለ

እነዚህ ተሽከርካሪዎች የሰው ህይወት ያጠፉ ንብረት ያጎደሉ ናቸው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በቅርቡ ባበለፀገው አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት ሲስተም በኩል የሁሉንም አሽከርካሪዎች መረጃዎችን እንደሚከታተልም አስታውቋል።

  የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር  አቶ  ክበበው ሚዴቅሳ ፤ ተቋሙ ሪፎርም ውስጥ እንደነበርም አንስተዋል።

ከሪፎርሞቹ አንዱ የቴክኖሎጂ ስራዎች አንዱ መሆኑን የሚናገሩት ዋና ዳይክተሩ፤ የትራፊክ ቁጥጥሩን ዘመናዊ ማድረግ እና ማሻሻል ደግሞ ዋነኛው ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ከጥር አንድ ጀምሮ ወደ ትግበራ የገባው  አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት እና ማኔጅመንት ሲስተም  የደንብ ጥሰት እንዲቀንስ፣
ለወረቀት ይወጣ የነበረውን  17 ሚሊየን ብር ማስቀረት መቻሉም ተገልጿል።

በከተማዋ ያሉ ተሽከርካሪዎች  እንዲሁም መንጃ ፍቃዳቸውም ከዚህ የሆኑ አሽከርካሪዎችም  በዚህ ሲስተም ውስጥ መግባታቸው የተነሳ ሲሆን ሁሉንም በዚህ ሲስተም መቆጣጠር መቻሉም ተነስቷል።

በዚህ ሲስተም ከክልል ወደ አዲስ አበባ የሚገባ ተሽከርካሪም ደንብ ሲተላለፍ ሲስተሙ እንደሚመዘግብም ተነስቷል።

ሲስተሙ ወደ ትግበራ ከገባበት ቀን ጀምሮም 2ሺ4 መቶ61  ደንብ ተላላፊዎች  በዚህ ሲስተም ተቀጥተዋል።

ከደንብ  ተላላፊዎቹ  1ሺ4 መቶ58  ቅጣት የተላለፈባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው መክፈልም ችለዋል።

7መቶ 72 ሺ 7 መቶ 40 የሚሆኑ አሽከርካሪዎች በዚህ አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት  ሲስተም ውስጥ መግባታቸውም ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ  ባለፉት 9 ወራት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ  ገቢ ከቅጣት  ማገኘቱንም ገልጿል።

ለዓለም አሰፋ

ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *