ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የትግራይ ክልል ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተኸልሽ ገ/ህይወት የነዳጅ ዕጥረት ችግር በክልሉ ካጋጠመ አምስት ወር መሆኑን ገልፀዋል።
ከጦርነቱ በፊት ይገባ የነበረው ነዳጅ መጠን በቀን ከ8 እስከ 16 ቦቴ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ግን በቀን ከ2 እስከ 3 ቦቴ ብቻ እየገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ምክንያት በአሁን ሰዓት በትግራይ ክልል ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ሰፊ ችግር እየገጠመዉ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የነዳጅ ችግር እንዲፈታ አንድ ዳይሬክተር ወደ አዲስ አበባ በመላክ ከሶስት ሳምንት በላይ ንግግር ቢደረግም የሚመለከተዉ አካል ምንም መፍትሄ እንዳልሰጣቸዉ ተናግረዋል።
የተወሰነ ነዳጅ ቢመጣም ለሚያስፈልጋቸው ለጤና ተቋማት እየሰጡ መሆኑን ገልፀው፤ አንዳንድ ድርጅቶች በነዳጅ እጥረት ምክንያት መስራት አለመቻላቸውንም ገልፀዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም
