ፊንቴክ ኢንቨስትመንት የኤሌክትሪክ መኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ 1.4 ቢሊዮን ብር ቀድመው ለተመዘገቡ 1ሺህ 2መቶ ደንበኞቹ ብድር ማመቻቸቱንም አስታውቋል።
ድርጅቱ 20ሺህ የቢ.ዋይ.ዲ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ የማምጣት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀስ መሆኑንም ሰምተናል።
የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ያብስራ ታደሰ ፤ድርጅቱ ለመኪናው ባትሪ የ8 ዓመት እንዲሁም በመኪናው አካል ላይ ለሚደርስ ጉዳት የ5 ዓመት ዋስትና ይሰጣል ሲሉም ተናግረዋል።
አቶ የአብስራ ታደሰ አክለውም ዘመናዊነትን በጠበቀ መልኩ የተፈጥሮ ሚዛን የሚጠብቅ ተሽከርካሪዎችን ለገበያው በማቅረብ የአለምን የሙቀት መጠን በአንድ ድግሪ ሰንቲግሬድ ለመቀነስ እየሰራ መሆኑም ገልፀዋል።
በአሁን ሰዓት ድርጅቱ በ9መቶ50 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ከወለድ ነፃ፤ ከአምስት አመት የእፎይታ ግዜ ጋር እያቀረበ ይገኛልም ተብሏል ።
በሦስት ዙር 2መቶ50 ተሽከርካሪዎችን አስረክበናል ያለው ድርጅቱ በአራተኛው ዙር ደግሞ 2መቶ 58 የቢ.ዋይ.ዲ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ መሆኑንም ተናግረዋል።
በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲና የፊንቴክ ኢንቨስትመንት አምባሳደር መንሱር ጀማል ጨምሮ አርቲስቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
ልኡል ወልዴ
ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም
