ሁለት መቶ አምስት ኢንደስትሪዎችን ደግሞ በገጠር ማቋቋም መቻሉ ተገልፆል።
ይህ የተባለዉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዘጠኝ ወራቱን የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነዉ።
ተቋሙ በተለያየ ምክንያቶች ስራ አቁመዉ የነበሩ አምራች ኢንደስትሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት መቻሉን ተናግሯል።
የኢንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በሰጡት የጋዜጣዊ መግለጫ ለዘርፉ ፈታኝ የሆነዉን የፋይናንስ አቅርቦት ለመፍታት ጥረት መደረጉን አንስተዋል።
6 ቢሊየን ብር ለአምራች ኢንተርፕራይዞች የቀረበ የስራ ማስኬጃ ብድር አቅርቦት ተሰቷል ተብሏል።
ከተወሰደዉ ዉስጥ 95 በመቶ ያህሉ የተወሰዱ ብድሮች መመለስ መቻላቸዉን ተቋሙ ገልጿል ።
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት በገጠር የኢንዱስትሪ መስፋፋት ላይ ስራዎች ነበሩት ያሉት አቶ አብዱል ፈታህ የሱፍ በዘጠኝ ወራቱ አፈፃፀም ለ 151 ሺህ ሰዎች የስራ እድል ፈጥረናል ብለዋል።
አዳዲስ ኢንደስትሪዎች በመክፈት ረገድ 2 ሺህ 7 መቶ ሀምሳ ሁለት ኢንደስትሪዎች ማቋቋም ችያለሁ ብሏል።
የአምራች ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር እያደረኩ ነዉ የሚለዉ ተቋሙ በዚህም በገበያ ትስስር እንዲገኝ ተሰርቷል ተብሏል።
የአምራች ኢንደስትሪዎችን ስራ በተመለከተም ከዉጪ ይገባ የነበረን ምርት በተኪ ምርቶች 1.6 ሚሊየን ዶላር ማዳን መቻሉን ከኢንተርኘራይዙ ሰምተናል።
በተቃራኒው 57 ሚሊየን ዶላር የዉጪ ምንዛሬ ምርቶችን በመላክ ማስገባት መቻሉን ተያያዞ በመግለጫዉ ተገልፆል።
ቁምነገር አየለ
ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
