ከከተማ ወደ ገጠር ተመላልሰው ሲያስተምሩ ለነበሩ ከ2ሺህ 5 መቶ በላይ መምህራን መኖሪያ ቤት ተመቻችቷል ተባለ

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በዘንድሮ በጀት አመት ከከተማ ወደ ገጠር ተመላልሰው ሲያስተምሩ ለነበሩ 2 ሺህ 9 መቶ 77 መምህራን መኖሪያ ቤት መመቻቸቱን አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህረት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶ/ር ካሳሁን ገላና ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ የመምህራን ጥቅማጥቅሞች ለማስጠበቅ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ በገጠር ለሚያስተምሩ መምህራን ቤት በመስራት በከተማ ላሉት ደግም ከክልሉና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመመካከር ቦታ የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ስራ እየተሰራ ነዉ ተብሏል።

ለመምህራኑ ቦታውን መስጠት የቻሉ ቢኖሩም ቦታዉን ያልሰጡ የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸዉን ሃላፊው ገልፀዋል።

የቢሮዉ ሀላፊ ዶ/ር ካሳሁን ሆኖም የመምህራን ጥቅም እንዲረጋገጥ እንደ ትምህርት ቢሮ ጥያቄዎች እያቀረብን ነው ብለዋል።

ልዑል ወልዴ

ሚያዚያ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *